am_tn/psa/005/007.md

1.2 KiB

በምሕረትህ (በታማኝነትህ) ብዛት

“ታማኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ገላጭ ሊተረጎም ይችላል። አማራጭ ትርጉም፤ “ለቃልኪዳንህ ታማኝ ስለሆንክ” (ረቂቅ ስምን ይመልከቱ)

ቤትህ

ይህ የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “ቤተ መቅደስህ”

በጽድቅህ ምራኝ

ዳዊት ጽድቅን አንደ መንገድ ማስተማርንም እንደ መምራት ይገልጻል፡፡ “ጽድቅህ” የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር ጻድቅ መሆኑን ያመለክታል አማራጭ ትርጉም፡ “ትክክል የሆነውን ማድረግ እንድችል አስችለኝ” (ምሳሌያዊ አባባልን ይመልከቱ)

መንገድህን በፊቴ አቅና

ዳዊት ጽድቅን እንደ መንገድ ይገልጸዋል። የቀና መንገድ ለማየትም ለመራመድም ቀላል ነው። አማራጭ ትርጉም፡ “በትክክለኛ መንገድ መኖርን አሳየኝ” ወይም “ትክክለ የሆነውን ማድረግ ቀላል አድርግልኝ” (ምሳሌያዊ አባባልን ይመልከቱ)