am_tn/psa/005/001.md

1.5 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ፡

በዕብራይስጥ ቅኔ ትይዩነት የተለመደ ነው፡፡ (ቅኔ እና ትይዩነትን ይመልከቱ)

ለመዘምራን አለቃ

“ይህ ለመዘምራን አለቃ ለአምልኮ እንዲጠቀምበት ነው”

በዋሽንት

“ይህ መዝሙር በዋሽንት በሚጠቀሙ መታጀብ አለበት”

የዳዊት መዝሙር

አማራጭ ፍችዎች፡ 1) ዳዊት ዝማሬውን ጽፎታል ወይም 2) ዝማሬው ስለዳዊት ነው ወይም 3) ዝማሬው የተዘመረው በዳዊት የአዘማመር ስልት ነው፡፡

ቃሌን አድምጥ

ይህ እርዳታን ፍለጋ የሚደረግ ጥሪ ነው፡፡ አማራጭ ትጉም፡ “ለእርዳታ ወደ አንተ ስጣራ ስማኝ”(ድብቅ ሃሳብ ወይም ግምታዊ እውቀትን ይመልከቱ)

መቃተቴን

ሰዎች በስቃይ ጊዜ የሚያሰሙት ዝግ ያለ ድምጽ

በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤ በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ

እነኚህ ሁለት ስንኞች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ (ትይዩነትን ይመልከቱ)

ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ

“ጥያቄዬን አቀርባለሁ” ወይም “የሚያስፈልገኝን እጠይቅሃለሁ”

በጥሞና እጠባበቃለሁ

“የጠየኩትን እንደምታደርግልኝ እጠብቃለሁ”