am_tn/psa/003/003.md

2.0 KiB

አንተ ግን ያህዌ ጋሻዬ ነህ

ጋሻ ተዋጊን ይከላከላል፡፡ ዳዊት እግዚአብሔርን እንደ ገሻው ይገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ አንተ ግን ያህዌ እንደ ጋሻ ትከልከኛለህ›› (ዘይቤን ይመልከቱ)

ክብሬ

እግዚአብሔርን ክብሬ ብሎ በመጥራት ዳዊት ክብር የሚሰጠው እግዚአብሔር እንደሆነ ይናገራል፡፡ ዳዊት ስለጠላቶቹ ስለተናገረ እና እግዚአብሔርን ጋሻዬ ስላለ፣ ክብሬ ሲል ደግሞ ምን አልባት በጠላቶቹ ላይ እንዲያሸንፍ በማድረግ ክብር እንደሚሰጠው ለማመልከት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ “ክብር የምትሰጠኝ አንተ ነህ” ወይም “ድልን የምትሰጠኝ አንተ ነህ” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

ራሴን ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ

“ራሴን ከፍ ክፍ የምታደርገው አንተ ነህ” አንድን ሰው ማበረታታት ራስን ከፍ እንደ ማድረግ ይገለጣል። አማራጭ ትርጉም “የምታበረታታኝ” (ዘይቤን ይመልከቱ)

ድምፄን ከፍ አደርጋለሁ

ለመጮህ ድምፅን መጠቀም ድምፅን ከፍ እንደማድረግ ይገለፃል፡፡ አማራጭ ጥርጉም፡ “እጮሃለሁ” (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

ሴላ

ይህ ምንአልባት ሰዎች እንዴት መዘመር ወይም የሙዚቃ መሳርያ እንዴት መጫወት እንደሚገባቸው የሚያሳይ የሙዚቃ ቃል ነው፡፡ አንድ አንድ ትርጉሞች የዕብራይስጥ ቃሉን ሲጽፉት ሌሎች ደግሞ በትርጉም ውስጥ እንደውም አያካትቱትም፡፡ በመዝ 3፡1 ይህን እንዴት እደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ (ቃላት መዋስን ይመልከቱ)