am_tn/psa/002/008.md

1.5 KiB

አያያዥ ዓረፍተ-ነገር፡

ያህዌ ለአዲሱ የእስራኤል ንጉሥ መናገሩን ይቀጥላ፡፡

ሕዝቡን ለርስትህ፣ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ

እነዚህ ሁለት ስንኞች አንድ አይነት ሃሳብን ያመለክታሉ፡፡ (ትይዩነትን ይመልቱ)

የምድርም ዳርቻ

‹‹እሩቅ የሚገኙ ቦታዎች››

በብረት በትር ትሰባብራቸዋለህ፤ እንደ ሸክላ ሰሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ

እነዚህ ሁለት ስንኞች አንድ አይነት ሃሳብን ያመለክታሉ፡፡ (ትይዩነትን ይመልቱ)

በብረት በትር ትሰባብራቸዋለህ

ሕዝቡን ማሸነፍ እንደ መሰበበር ተገልጧል የንጉሡም ኃይል እንደ ብረት ተገልጧል፡፡ አማራጭ ትርጉም፤ ‹‹በኃይልህ ሙሉ ለሙሉ ታሸንፋቸዋለህ፡፡›› (ዘይቤን ይመልከቱ)

ትቀጠቅጣቸዋለህ

ሕዝቦችን መሸነፍ እንደ ሸክላ ዕቃ መሰባበር ተገልጧል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ ‹‹ሙሉ ለሙሉ እንደ ሸክላ ዕቃ ታጠፋቸዋለህ›› (ዘይቤን እና አነጻጻሪ ዘይቤን ይመልክቱ)

እንደ ሸክላ ሰሪ ዕቃዎች

የሸክላ ሰሪ ዕቃዎች በቀላሉ ተሰባሪ ዕቃዎች ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ ‹‹ሸክላ›› ወይም ‹‹የሸክላ ዕቃ›› (የማይታወቁን መተርጎምን ይመልክቱ)