am_tn/psa/002/001.md

2.2 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ፡

ትይዩነት በዕብራይስጥ ቅኔ የተለመደ ነው፡፡ (ቅኔ እና ትይዩነትን ይመልከቱ)

አሕዛብ ለምን አጉረመረሙ፣ ሕዝቦችስ ለምን ከንቱ ሴራ ያሴራሉ?

እነዚህ ጥያቄዎች የተጠየቁት ሕዝቡ ምን ያህል የተሳሳተ እና የሞኝ ነገሮች እንደሚያደርጉ ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ ‹‹አሕዛብ ግራ ተጋብተዋል ሕዝቦችም ከንቱ ሴራ ያሴራሉ›› (መልስ አዘል ጥያቄዎችን ይልከቱ)

አሕዛብ ለምን ያጉረመርማ

ይህ የሚያመለክተው ምንአልባት አሕዛብ የንዴት ጩኸት እያሰሙ እንደነበር ነው፡፡

አሕዛብ

ይህ የሚወክለው መሪዎቹን ወይም ሕዝቦቹን ነው፡፡ (ድጋሚ መሰየምን ይመልከቱ)

ከንቱ ሴራ

ምን አልባት በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ ላይ የተሴረ ሴራ ነው፡፡

የምድር ነገሥታት ተነሱ፤ አለቆችም … እንዲህ ሲሉ ተማከሩ

እነኚህ ሁለት ስንኞች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ (ትይዩነትን ይመልከቱ)

ተነሱ … ተማከሩ

እነዚህ ቃላት አንድ ዓይነት ትርጉም አላቸው፡፡ የሚያመለክቱም፤ መሪዎች በአንድ ላይ እግዚአብሔርን እና መሲሁን ለመዋጋት እንደ ተነሱ፡፡ ይህ በግልጽ ሊፃፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፤ ‹‹ለመዋጋት መሰባሰብ … ለማመጽ በጋራ ማቀድ›› (ድብቅ ሃሳብ ወይም ግምታዊ እውቀትን ይመልከቱ)

መሳርያቸውን እንበጥስ… ገመዳቸውንም እንጣል

ሌሎች ሕዝቦች ስለ የያህዌን እና የመሲሁን በእነርሱ ላይ መንገስ እንደ መሳርያ እና ሰንሰለት ይገልጹታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ ‹‹ከእነርሱ ቁጥጥር ራሳችንን ነፃ ማውጣት አለብን፤ በእኛ ላይ እንዲሰለጥኑ ልንፈቅድላቸው አይገባም›› (ዘይቤን ይመልከቱ)