am_tn/psa/001/003.md

1.3 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ

ይህ ክፍል አንድ ጻድቅ ሰው ምን እንደሚመስል አንድ በአበበ ዛፍ ምስል ያብራራል፡፡

እርሱም … ፍሬዋን በየጊዜው እንደምትሰጥ ዛፍ ነው

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ አንድ ጊዜ ሰዎች እንደ ዛፍ ይመሰላሉ፡፡ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ የሚሰኙ ሰዎች እግዚአብሔር እንዲሰሩ የሚፈልውን ሁሉ በውሃ ዳር የተተከለ ዛፍ መልካም ፍሬን እንደሚያፈራ መስራት ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፤ “ዛፍ በየወቅቱ እንደሚያራ የበለጸገ ይሆናል” (አነጻጻሪ ዘይቤን ይመልከቱ)

በውሃ ዳር እንደተተከለ

ከውሃ ዳር የተተከለ ዛፍ ጤነኛ ሆኖ እንዲቆይ የሚያደርገውን የውሃ መጠን ያገኛል፡፡

ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ

ጤነኛ ዛፎች መልካም ፍሬን በወቅቱ ያፈራሉ፡፡

ቅጠልዋም እንደማይረግፍ

በቂ ውሃ የሚያገኝ ዛፍ ቅጠሎቹ ደርቀው አይሞቱም፡፡

የሚሰራው ሁሉ ይከናወንለታል

“በሚሰራው ሁሉ ስኬታማ ይሆናል”