am_tn/psa/001/001.md

1.9 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ፡

በዕብራይስጥ ቅኔ ትይዩነት የተለመደ ነው፡፡ (ቅኔ እና ትይዩነትን ይመልከቱ)

በክፉዎች ምክር ያልሄደ

የ“ክፉዎች ምክር” የቀረበው እንደ መንገድ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፤ “በክፉዎች ምክር ያልሄደ” ወይም “የክፉዎችን ምክር ያልተገበረ” (ዘይቤን ይመልከቱ)

በኃጢአተኞች መንገድ የልቆመ

እዚህ ጋር “መንገድ” የሚለው ቃል የሚወክለው የሰዎችን የአኗኗር ዘይቤ ነው፡፡ “መቆም” የሚለው ቃል ደግሞ “መራመድ” ከሚለው ቃል ጋር ትይዩ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፤ “የኃጢአተኞችን ባህሪ ማስመሰል”፡፡ (ዘይቤን ይመልከቱ)

ወይም በዋዘኞች መንገድ ያልተቀመጠ

በእግዚአብሔር ላይ ከሚያፊዙ (ዋዘኞች) ጋር መቀመጥ የሚያመለክተው ከዋዘኞች ጋር ማበርን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፤ “ከዋዘኞች ጋር ማበር” ወይም “ከሌሎች ፊዘኞች ጋር እግዚአብሔር ላይ ማፊዝ”፡፡ (ድጋሚ መሰየም (Metonymy)ን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል

“መደሰት” የሚለው ቃል ከረቂቅ ስም የወጣ ግስ ነው፡፡ አንድ ግለሰብ በሕግ ሊደሰት ይችላል ማለትም ሕጉ መልካም ስለሆነ እና ስለሚታዘዘው ደስተኛ ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጉም፤ “የእውነት የሚያስደስተው የእግዚአብሔር ሕግ ነው” ወይም “የእውነት የሚያስደስተው የእግዚአብሔርን ሕግ አየታዘዘ እንደሆነ ማወቁ ነው” (ረቂቅ ስምን ይመልከቱ)