am_tn/pro/31/30.md

2.1 KiB

ቁንጅና አሳሳች ነው

“ቁንጅና” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቆንጆ ሴት ሰዎችን ልታታልል ትችላለች” ወይም “መልካም ውበት ያላት ሴት በእርግጠኝነት ክፉ ልትሆን ትችላለች፡፡” ይህንን በምሳሌ 11:16 እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ውበትም ጠፊ ነው

“ውበት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አሁን ውብ የሆነች ሴት ሁልጊዜ ውብ ልትሆን አትችልም” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እርሷ ትመሰገናለች

ይህ በገቢር ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ያመሰግኗታል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የእጆቿን ፍሬ

ከሱፍ እና ከተልባ እግር (ምሳሌ 31:13) ስራ ያገኘችው ገንዘብ ፍሬ ከሚሰጥ ዛፍ እነንደሚገኝ ፍሬ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ እጆች ለሰውየው ተዛምዶአዊ ዘይቤ ነው፡፡ ይህንን በምሳሌ 31:16 እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ያገኘችው ገንዘብ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ስራዋቿም በአደባባዮች ያስመሰግኗት

ስለ ሰራችው ስራዎቿ ትመሰገናለች፣ በስራዎቿ አይደለም፡፡ “በአደባባይ” ያሉት ሰዎች ንግድና የሕግ ጉዳዮች በከተማይቱ መግቢያ አካባቢ የሚሰሩ የከተማይቱ ዋነኛ ሰዎች ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሰራችው ስራዎቿ ምክንያት የከተማይቱ ዋነኛ ሰዎች ያመስግኗት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)