am_tn/pro/31/26.md

1.7 KiB

አፏን በጥበብ ትከፍታለች

አፋችንን የመክፈት ተግባር ለመናገር ምትክ ስም ነው፡፡ ”ጥበብ” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ተውሳከ ግስ ወይም ቅጽልሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጥበብ ትናገራለች” ወይም “የጥበብ ቃላት ትናገራለች” (ምትክ ስም እና ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የደግነት ሕግም በምላሷ ላይ አለ

“በምላሷ ላይ” የሚለው ሀረግ ንግግሯን የሚያመለክት ነው፣ ምክንያቱም ምላስ የአፍ አንዱ አካል ነው፡፡ “የደግነት ሕግ” የሚለው ሀረግ ሰዎችን ደግ እንዲሆኑ ማስተማርን የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ደግ እንዲሆኑ ታስተምራለች” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የቤተሰቦቿን መንገዶች ትመለከታለች

“መንገዶች” የሚለው ቃል ሰዎች የሚኖሩበትን መንገድ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቤተሰቦቿ በሙሉ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እየኖሩ እንደሆነ ታረጋግጣለች” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የስንፍናንም እንጀራ አትበላም

የአንድ ነገር “እንጀራ መብላት” አንድ ነገር መስራት ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰነፍ አይደለችም” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ስንፍና

ምንም አለመስራት እና ሰነፍ መሆን