am_tn/pro/31/08.md

1.4 KiB

መናገር ለማይችሉ ተናገርላቸው

መናገር ንጹሐን ሰዎችን ለመከላከል ለምንጠቀምባቸው ቃላት ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ራሳቸውን መከላከል ለማይችሉ አንተ ተከላከልላቸው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እየጠፉም ላሉት ሁሉ ስለ ጉዳያቸው ተናገር

ስለ ጉዳያቸው የሚለው ጉዳይ ያለበትን ሰው የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለዚህ ሰዎች በፍትህ ምክንያት እየጠፉ ያሉትን በአግባቡ እንዲይዙአቸው” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ስለ ጉዳያቸው

ይህ አስጨምሬ ሊሞላ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለ ጉዳያቸው ተናገር” ወይም “ስለ እነርሱ ተናገር” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ድሆችና የተቸገሩ ሰዎች

እነዚህ ሁለት ቃላት በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ በአንድ ላይ ጥቅም ላይ የዋሉት ደግሞ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ድሃ የሆኑና የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማግኘት የማይችሉ ሰወች” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)