am_tn/pro/31/01.md

2.2 KiB

ንጉስ ልሙኤል

ይህ የንጉስ ስም ነው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

ልጄ ሆይ፣ ምንድን ነው? የማሕጸኔ ልጅ ሆይ ምንድን ነው? የስእለቴ ልጅ ሆይ ምን ፈለግህ?

የዚህ “ምን” የሚለው መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ምን ትሰራለህ?” ወይም “የምትሰራውን ልትሰራው አይገባም” ወይም 2) “ምን ልንገርህ?” ወይም “የምነግርህን ስማኝ” ወይም 3) “እንዳታደርግ የማስጠነቅቅህን ነገሮች አትስራ” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ልጄ … የማሕጸኔ ልጅ … የስእለቴ ልጅ

ጸሐፊው አድማጩ በጥንቃቄ እንዲያስተውልና ለሚናገረው ሰው አክብሮት እንዲሰጥ ይፈልጋል፡፡

የማሕጸኔ ልጅ

ማህጸን ለሰውየው ተዛምዶአዊ ዘይቤ ነው፡፡ ልጆች ከመወለዳቸው በፊት ለሚያድጉበት ለሰውነት ክፍል የበለጠ ትህትና ያለው ቃል መጠቀም ተመራጭ ነው፡፡

የስእለቴ ልጅ

“ስእለት” የሚከተሉትን ሊሆን ይችላል፡- 1) የእናት የጋብቻ ቃል ኪዳን ወይም 2) ካገባች በኋላ እግዚአብሔር ልጅ እንዳተገኝ የፈቀደላት ከሆነ ልጇን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ቃል የገባችው፡፡

ብርታትህን ለሴቶች አትስጥ

ከትዳር ውጭም ሆነ ከቁባቶች ጋር “ከሴቶች ጋር ወሲብ ለመፈጸም ብዙ አትድከም፡፡

ነገስታትን ለሚያጠፉም መንገድህን

“ወይም ነገስታትን የሚያጠፉ ሰዎች እንዲመክሩህ ፍቀድላለቸው”

መንገድህ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ሕይወትህን የምትኖርበት መንገድ” ወይም 2) “የምትሰራው ስራ”

ነገስታትን ለሚያጠፉም

ምናልባት ብርታቱን ሊሰጣቸው የማይገቡ ስነ-ምግባር የሌላቸው “ሴቶች”