am_tn/pro/29/25.md

1.8 KiB

ሰውን መፍራት ወጥመድ ውስጥ ይከትታል

ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን በማሰብ መፍራት በወጥመድ ውስጥ እንደመግባት ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን በማሰብ የሚፈራ ሰው በወጥመድ ውስጥ እንደተየያዘ ሰው ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወጥመድ

እንስሳትን በገመድ አፍኖ የሚይዝ

በእግዚአብሔር የሚታመን ይጠበቃል

ይህ በገቢር ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር በእርሱ የሚታመነውን ይጠብቀዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ብዙዎች የገዢን ፊት ይፈልጋሉ

“ፊት” የሚለው ቃል ሕዝቡ እርሱ ሊያደርግላቸው የሚፈልጉት ነገር ምን እንደሆነ ሲነግሩት የሚሰማና ሰምቶም የሚፈጽም መሪን የሚወክል ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ብዙ ሕዝብ መሪያቸው ለእነርሱ ትኩረት እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ፍትህ ለሰው የሚመጣው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው

ሰዎች አንድን ሰው በፍትህ ይዘው እንደሆነና እንዳልሆነ የሚመለከት እግዚአብሔር እንጂ የሰው መሪዎች አይደሉም፡፡ “ፍትህ” የሚለው ረቂቅ ስም “ፍትሀዊ” ተብሎ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሰዎች እውነተኛ ፍትሀዊ የሆነ እግዚአብሔር ነው” (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)