am_tn/pro/29/23.md

1.7 KiB

ትሁት መንፈስ ያለው ሰው ክብር ይሰጠዋል

ይህ በገቢር ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትሁት መንፈስ ላለው ሰው ሰዎች ክብር ይሰጡታል” ወይም “ትሁት መንፈስ ያለው ሰው ከሰዎች ክብር ይቀበላል” ወይም “ትሁት መንፈስ ላለው ሰው እግዚአብሔር ሰዎች እንዲያከብሩት ያደርጋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የራሱን ሕይወተት ይጠላል

“የራሱ ጠላት ይሆናል”

እርግማንን ይሰማል መልስ ግን አይሰጥም

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ከሌባ ጋር የሚካፈል ሰው” ስለሚያውቀው ነገር ማለትም ሌባው ስለሰረቀው ነገር እውነቱን እንዲናገር ሰዎች በመኃላ ስር ይይዙታል፣ እርሱም እውነቱን ቢናገር እንደሚቀጣ ያውቃል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በመኃላ ለመመስከር ፈቃደኛ አይሆንም” ወይም 2) ሰዎች ሌባው ማን እንደሆነ አያውቁም ነገር ግን ሌባው እንዲረገም ወደ እግዚአብሔር ይጮሃሉ፣ ከዚያም “ከሌባው ጋር የተካፈለው” ሰው ለመናዘዝ ይፈራል ስለዚህ ከእርግማኑ ይወጣል ምክንያቱም ሌባውን ስለሚፈራ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ከረገሙት በኋላ እንኳ መልስ አይሰጥም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)