am_tn/pro/29/15.md

1.9 KiB

በትርና ተግሳጽ ጥበብን ይሰጣሉ

ጸሐፊው በትርና ተግሳጽ እንደ ቁሳዊ እቃ ጥበብን የሚሰጡ ሰዎች አንደሆኑ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወላጅ ልጁን ለመቅጣት በትር ቢጠቀምና ቢገስጸው፣ ልጁ ጥበበኛ ይሆናል” ወይም “ወላጆች ልጃቸውን ቢቀጡና ጥፋት ሲሰራ ቢነግሩት ልጁ በጥበብ መኖርን ይማራል” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በትር

በእስራኤል የነበሩ ወላጆች ልጆቻቸውን በመምታት ስነ ስርዓት ለማስያዝ የእንጨት በትር እንደ መሳርያ ይጠቀሙ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስነ ስርዓት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ተግሳጽ

አንድ ሰው ለሌላ ሰው ተግሳጽ ሲሰጥ ወይም ያንን ሰው ሰገስጽ እርሱ የሚሰራውን ስራ እንደማይቀበለው ለዚያ ሰው እየነገረው ነው፡፡

አመጸኝነት ይጨምራል

ይህ “አመጸኝነት” የሚለው ረቂቅ ቃል እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ተጨማሪ ሰዎች አመጽን ያደርጋሉ ከዚያም ኃጢአታቸው እየበዛ ይመጣል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የክፉ ሰዎች ውድቀት

“ውድቀት” የሚለው ረቂቅ ስም “ወደቀ” በሚለውና የመምራት ስልጣንን ለማጣት ተለዋጭ ዘይቤ በሆነው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ ክፉ ሰዎች ይወድቃሉ” ወይም “እነዚህ ክፉ ሰዎች የመሪነት ስልጣናቸውን ያጣሉ” (ረቂቅ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)