2.9 KiB
ሰው
“ያ ሰው”
ድሀ
ይህ በአጠቃላይ ድሆችን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ድሀ ሰዎች” (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)
ምንም አያጡም
ይህ ድርብ አሉታዊ ቃላት ጥቅም ላይ የዋለው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚያስፈልጋቸው ማንኛውም ነገር አላቸው” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)
በእነርሱ ላይ ዓይኖቹን የሚከድን ሰው ብዙ እርግማን ይቀበላል
ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ከድሀው ብዙ እርግማ ይቀበላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ድሆች በእነርሱ ላይ ዓይናቸውን ለሚከድኑ ለማንኛውም ሰው ብዙ እርግማ ይሰጣሉ” ወይም 2) በአጠቃላይ ብዙ እርግማን ከሰዎች ይቀበላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች በድሆች ላይ ዓይናቸውን ለሚከድኑ ለማንኛውም ሰው ብዙ እርግማን ይሰጣሉ” ወይም 3) ከእግዚአብሔር ብዙ እርግማን ይቀበላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር በድሆች ላይ ዓይናቸውን ለሚከድኑ ለማንኛውም ሰው ብዙ እርግማን ይሰጣቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
ዓይኖቹን የሚከድን
“ዓይኑን የሚገድን ማንኛውም ሰው”
ለ … ዓይኖቹን የሚከድን
ዓይንን መክደን ለድሆች ፍላጎት ምላሽ አለመስጠትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቸል የሚል” ወይም “ላለመርዳት መምረጥ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
ክፉ ሰዎች ሲነሱ
ይህ ፈሊጥ ሲሆን ክፉ ሰዎች ስልጣን ሲይዙ ወይም መግዛት ሲጀምሩ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎች ወደ ስልጣን ሲወጡ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)
ሰዎች ራሳቸውን ይሸሽጋሉ
ክፉ ሰዎች እነርሱን እንዳይጎዱአቸው ሊያደርጉ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረጋቸው በግነት የቀረበ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ወደ መሸሸጊያ ይሄዳሉ” (ግነትና ጅምላ ፍረጃ እና ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ አመልካች ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ))
ይጠፋሉ
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ይሄዳሉ” ወይም 2) “ከስልጣን ይወርዳሉ” ወይም 3) “ይወድማሉ፡፡”
ይጨምራሉ
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ይበዛሉ” ወይም 2) “ወደ ስልጣን ይወጣሉ፡፡”