am_tn/pro/28/21.md

1.3 KiB

ለቁራጭ ዳቦ ሲል ሰው ስህተትን ይሰራል

እዚህ ላይ “ቁራጭ ዳቦ” የሚለው በጣም ትንሽ ጉቦ ወይም ስጦታ ለማሳየት ጥቅም ላይ የዋለ ግነት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰው ለትንሽ ጥቅም ሲል ኃጢአትን ይሰራል” (ግነትና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ስህተት ይሰራል

“ኃጢአት”

ስስታም ሰው

“ራስ ወዳድ ሰው፡፡” ይህ ያለውን ሀብት ለሌሎች ለማካፈልና ገንዘብ ለማውጣት የማይወድ ሰው ነው፡፡

ሀብት ያሳድዳል

ስስታም ሰው ሀብት እንደሚያሳድድ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሀብት በጣም ስስታም ነው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ድህነት በእርሱ ላይ ይመጣል

የስስታምነት ውጤት ድህነት በስስታም ላይ በድንገት እንደሚደርስበት ተደርጎ ተነግሯል፡፡ “ድህነት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በድንገት ድሃ ይሆናል” (ፈሊጥ እና ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)