am_tn/pro/28/19.md

2.0 KiB

መሬቱን የሚያርስ

ይህ መሬቱን የሚያርስ፣ የሚዘራ እና ሰበሉን የሚንከባከብ ማለት ነው፡፡

የሚከተል

“የሚከተል ማንኛውም ሰው”

የማይጠቅም ሞያ የሚከተል

“የማይጠቅም ሞያ ያሳድዳል፡፡” ምንም ትርፍ የሌላቸውን ነገሮች በመስራት የሚደክምና ጊዜ አልባ የሚሆን ሰው የማይጠቅሙ ነገሮችን እንደሚያሳድድ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

በድህነት ይሞላል

የማይጠቅሙ ሞያዎችን የሚከተል ሰው የተትረፈረፈ ምግብ እንደማያገኝ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ “ድህነት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “will be very poor” (ምፀት እና ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ))

በጥድፊያ ሃብታም የሆነ ግን ሳይቀጣ አይቀርም

“ሳይቀጣ አይቀርም” የሚለው ሁለት አሉታዊ አገላለጽ ጥቅም ላይ የዋለው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጥድፊያ ሃብታም የሚሆኑትን ሰዎች እግዚአብሔር በእርግጠኝት ይቀጣል” (ምፀት እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በጥድፊያ ሃብታም የሆነ

እዚህ ላይ ያለው አመልካች መረጃ ይህ ሰው ሀብት ያገኘው ታማኝነት በጎደለውና አታላይነት በተሞላበት መንገድ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጠድፊያ ሀብታም ለመሆን የሚሞክር ሰው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)