2.2 KiB
የሌላ ሰው ደም አፍስሷል
እዚህ ላይ “ደም” የሚለው የሰውን ሕይወት ይወክላል፡፡ “ደምን ማፍሰስ” አንድን ሰው መግደል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሆነ ሰው ገድሏል” ወይም “የሆነ ሰውን ነፍስ አጥፍቷል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
ኮብላይ
እንዳይያዝ ለማምለጥ የሚሸሽ ሰው
እስከ ሞት ድረስ
“እስከሚሞት ድረስ፡፡” ለቀጣይ የሕይወቱ ዘመን ሁሉ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕይወቱን በሙሉ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)
በሐቀኝነት የሚራመድ ሰው በደህና ይጠበቃል
ይህ በገቢር ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአበሔር በሐቀኝነት የሚሄድን ማንኛውንም ሰው በደህንነት ይጠብቀዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
ማንም
“ማንኛውም ሰው”
በሐቀኝት የሚራመድ
ይህ የሐቀኝነት ሕይወት የሚኖር ሰው የሚወክል ነው፡፡ “ሐቀኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ተውሳከ ግስ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በታማኝነት ይራመዳል” ወይም “በታማኝነት ይኖራል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
መንገዱ በጠማማነት የተሞላ
ታማኝ ያልሆኑ ባለጠጋ ሰዎች በጠማማ መንገድ ወይም በጠመዝማዛ መንገድ እንደሚሄዱ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በታማኝነት የማይኖር ሰው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
በድንገት ይወድቃል
ታማኝ ባልሆነ ሰው የሚደርሰው ነገር በድንገት እንደሚወድቅ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በድንገት ይጠፋል” ወይም “በድንገት ይከስራል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)