am_tn/pro/28/15.md

1.8 KiB

እንደሚያገሳ አንበሳ ወይም እንደ ተቆጣ ድብ በድሆች ላይ የሚገዛ ክፉ ገዥም እንዲሁ ነው

ከክፉ ገዥ ሊያድናቸው የሚችል ማንም የሌላቸው ድሃ ሰዎች አንበሳ በላያቸው ላይ ከሚያገሳባቸው ሰዎች ወይም ድብ ከሚያጠቃቸው ሰዎች ጋር ተነጻጽረዋል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የተቆጣ ድብ

ድብ በአራት እግር የሚራመድ ስለታም ጥፍርና ጥርስ ያለው ትልቅ፣ አስፈሪና አደገኛ እንስሳ ነው፡፡ (የማይታወቁ ነገሮችን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

ማስተዋል የሌለው ገዥ

“ማስተዋል” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የማያስተውል ገዥ” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ጨቋኝ

ሰዎችን በማስጨነቅ የሚይዝና የሰዎችን ሕይወት አሰቃቂ የያደርግ

ማታለልን የሚጠላ ሰው

“ማታለል” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ታማኝ አለመሆንን የሚጠላ ሰው” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እድሜውን ያረዝማል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ይህ ፈሊጥ ሲሆን ለበለጠ ጊዜ ይኖራል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ረጅም ጊዜ መኖር” ወይም 2) ይህ ፈሊጥ ሲሆን የመሪነት ጊዜውን ማስረዘም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለረጅም ጊዜ ይመራል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)