am_tn/pro/28/13.md

2.3 KiB

ኃጢአቱን ይደብቃል

“ኃጢአቱን ይሰውራል፡፡” ይህ ንስሃ የመግባትና ኃጢአትን የመተው ተቃራኒ ሲሆን ኃጢአትን ወደ ብርሃን ከማምጣት ይልቅ ኃጢአትን መሰወር ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አይበለጽግም

“አይሳካለትም” ወይም “አያድግም”

ኃጢአቱን የሚሰውር አይሳካለትም፣ የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምህረትን ያገኛል

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ለሚናዘዙና የሚተወው ምህረትን ይሰጣቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ዘወትር እግዚአብሔርን እየፈራ የሚኖር ሰው ደስተኛ ነው

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ዘወትር እየፈራ የሚኖርን ሰው ይባርካል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እየፈራ የሚኖር ሰው

“መፍራት” የሚለው ረቂቅ ስም አንደ ቅጽል ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በፍርሃት የተሞላ ሕይወት ይኖራል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

መፍራት

ይህ እግዚአብሔርን በጥልቀት ማክበርና ይህንን አክብሮት እርሱን በመታዘዝ ማሳየትን ያመለክታል፡፡

ልቡን የሚየጠነክር ሰው

“ልቡን የሚያደነድን ሰው”

ልቡን አጠነከረ

ይህ ፈሊጥ ሲሆን ግትርና እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ያልሆነ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ፈቃደኛ አይደለም” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

መከራ ውስጥ ይወድቃል

ይህ በስቃይና በጉስቁልና ውስጥ መግባትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በችግር ውስጥ ይገባል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)