am_tn/pro/28/11.md

2.2 KiB

በራሱ ዓይኖች ጥበበኛ ሊሆን ይችላል

ዓይኖች መመልከትን ይወክላል፣ መመልከት ደግሞ ሃሳብንና ግንዛቤን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በራሱ አስተሳሰብ ጥበበኛ ነው” ወይም “ጥበበኛ እንደሆነ ያስባል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ማስተዋል ያለው

“ማስተዋል” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግስ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚያስተውል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱን ይመረምረዋል

ይህ ፈሊጥ ሲሆን ድሃው ሰው ሀብታምን ሰው በእርግጥ ጥበበኛ እንደሆነና እንዳልሆነ መወሰን ይችላል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እውነተኛ ተፈጥሮውን ይመለከታል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ጽድቅን የሚያደርግ ድል በሚያገኙበት ጊዜ

“ጽድቅን የሚያደርግ በሚሳካለት ጊዜ”

ክፉዎች በሚነሱበት ጊዜ

ይህ ፈሊጥ ሲሆን ክፉ ሰዎች ስልጣን በሚይዙበት ጊዜ ወይም መምራት በሚጀምሩበት ጊዜ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎች ወደ ስልጣን በሚመጡበት ጊዜ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉ ሰው

ይህ በአጠቃላይ ክፉ ሰዎችን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎች” (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)

ሰዎች ራሳቸውን ይሸሽጋሉ

እነዚህ “ራሳቸውን የሸሸጉ” ሰዎች ከክፉ ሰዎች ለማምለጥ ሲሉ ራሳቸውን መደበቃቸውን ግልጽ ማድረግ ያስፈልግ ይሆናል፡፡ ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎችን ያገኙአቸዋል” ወይም “ከእነርሱ የተደበቁትን ሰዎች ያገኙአቸዋል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)