2.5 KiB
አንድ … ከሆነ
“አንድ ሰው … ከሆነ”
ሕግን ከማድመጥ ጆሮውን የሚያዞር ከሆነ
ይህ ሰው በሁለንተናው የእግዚአብሔርን ሕግ ከማድመጥ ጆሮውን ማዞርና አለመቀበልን የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእግዚአብሔርን ሕግ ከማድመጥና ከመታዘዝ ይዞራል” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሎቱ እንኳ የተጠላ ነው
“ጸሎቱ እንኳ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው፡፡” ይህ በገቢር ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ጸሎቱን እንኳ ይጠላዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
የጠጠላ
ይህንን በምሳሌ 3:32 እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡
ቅኑን ሰው ወደ ክፋት መንገድ የሚመራ ሁሉ
ይህ ቅን ሰዎችን ወደ ክፋት መንገድ ለመምራት ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቅኑን ሰው ወደ ክፋት መንገድ እንዲሔድ የሚያደርግ ሁሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ወደ ክፋት መንገድ የሚመራ ሁሉ … ይወድቃል
“አንድ ሰው ወደ ክፋት መንገድ ከመራ … ይወድቃል”
ቅን
ይህ በአጠቃላይ ቅን ሰዎችን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቅን ሰዎች” (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)
በቆፈረው ጉድጓድ ይገባል
“ራሱ በቆፈረው ወጥመድ ውስጥ ይገባል፡፡” ፍጻሜው ሌሎችን ወደመራበት ተመሳሳይ መጥፎ ቦታ ስለመሆኑ የሚያመለክት ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ሌሎች ሰዎቸን ወደመራበት ክፉ ስፍራ የእርሱም ፈጻሜ እንደዚያው ይሆናል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ንጹሐን ሰዎች
ይህ በአጠቃላይ ነቀፌታ የለለባቸውን ሰዎች የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነቀፌታ የሌለባቸው ሰዎች” (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)
መልካምን ነገር ይወርሳሉ
“መልካም የሆነውን ነገር ይወርሳሉ”