am_tn/pro/28/05.md

2.2 KiB

ክፉ ሰዎች

እዚህ ላይ “ሰዎች” የሚለው በአጠቃላይ ሕዝብ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ነገሮችን የሚሰሩ ሕዝብ” (ለወንዶች የምንጠቀምባቸው ቃላቶች ሴቶችንም ሲያካትቱ የሚለውን ይመልከቱ)

ፍትህን አያውቁም

“ፍትህ” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ፍትህ ምን እንደሆነ አታውቅም” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚብሔርን የሚፈልጉ ሰዎች

እግዚአብሔርን ለማወቅ የሚፈልጉና እርሱን የሚያስደስቱ ሰዎች እግዚአብሔርን በአካል ለማግኘት እንደሚፈልጉ ተደርገው ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉን ነገር ያውቃሉ

ከዚህ የምናገኘው አመልካች መረጃ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ ፍትህ ሁሉን ነገር ያውቃሉ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ፍትህ ምን እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ያውቃሉ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከባለጠጋ ይልቅ … ድሃ ሰው ይሻላል

“ባለጠጋ ሰው ከመሆን ይልቅ … ድሃ ሰው መሆን ይሻላል

በሐቀኝነት የሚራመድ

ይህ የሐቀኝትን ሕይወት የሚኖር ሰውን ይወክላል፡፡ ይህ “ሐቀኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ተውሳከ ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በታማኝነት ይራመዳል” walks honestly” or “lives honestly” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በመንገዱ ጠማማ የሆነ

ታማኝ ያልሆኑ ባለጠጋ ሰዎች በጠማማ መንገድ ወይም በጠመዝማዛ መንገድ እንደሚሄዱ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሚያደርገው ነገር ታማኝ ያልሆነ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)