am_tn/pro/27/23.md

1.4 KiB

የመንጋህን ሁኔታ በእርግጠኝነት እወቅ፣ ስለ እንስሳዎችህም ግድ ይበልህ፣

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ በአንድ ላይ የተቀመጡት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

መንጋህ

“የበግ መንጋ”

እንስሳዎችህ

“የፍየል መንጋ”

ዘውድ ለትውልድ ሁሉ ይጸናልን?

ይህ ጥያቄ የምድር ገዢዎች የአገዛዝ ዘመን ለዘላለም እንደማይኖር ግንዛቤ ለማስጨበጥ አሉታዊ መልስ የሚሰጥበት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ይህ እንደ ዓረፍተ-ሃሳብ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ዘውድ ለትውልድ ሁሉ አይጸናም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ዘውድ

እዚዚ ላይ “ዘውድ” የንጉሱን በመንግስቱ ላይ ያለውን አገዛዝ የሚያሳይ ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የንጉስ አገዛዝ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

አዲሱ ቡቃያ አድጎ ይታያል

“አዲስ ቡቃያ ይታያል” ወይም “አዲስ ሳር ማደግ ጀምሯል”