am_tn/pro/27/21.md

2.0 KiB

ማቅለጫ ለብር ከውርም ለወርቅ ነው

ይህ ወርቅና ብር እንዴት እንደሚነጥሩ የሚያሳይ ነው፡፡ ብረት መቅለጥ እንዲችልና በውስጡ ያለው ቆሻሻ እንዲወገድ የሚነጥረው እጅግ በጣም ሀይለኛ በሆነ የሙቀት ሃይል በማሞቅ ነው፡፡ ይህን በጣም ተመሳሳይ ሀረግ በምሳሌ 17:3 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- አማራጭ ትርጉም፡- “ማቅለጫ ብር ለማንጠር ይጠቅማል፣ ከውር ደግሞ ወርቅ ለማንጠር ይጠቅማል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ማቅለጫ

በጣም ከፍተኛ በሆነ ሙቀት ብረት የሚቀልጥበት ማሰሮ ነው፡፡ (የማይታወቁ ነገሮችን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

ከውር

ከመጠን በላይ ማሞቅ የሚቻል ምድጃ (የማይታወቁ ነገሮችን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

ሰውም በሚመሰገንበት ጊዜ ይፈተናል

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው ሌላ ሰው ሲያመሰግን ያንን ሰው እየፈተኑት ነው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ሞኝን ብትወቅጠውም … ሞኝነቱ ግን እርሱን አይለቀውም

ምንም እንኳ ሞኝ በብዙ መከራ ወይም ውጣ ውረድ ቢያልፍም (መወቀጥ በዕብራይስጥ ብዙ ጊዜ ለመከራ ተለዋጭ ዘይቤ ነው) ሞኝ እንደሆነ ይቀራል ማለት ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዘነዘና

የተለያዩ ነገሮችን በሙቀጫ ለማድቀቅ የሚረዳ ክብ ጫፍ ያለው ጠንካራ መሳርያ ነው (የማይታወቁ ነገሮችን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)