am_tn/pro/27/15.md

1.7 KiB

ጠበኛ

ይህ ሰዎች እርስ በርሳቸወ እንዲበሳጩ ማድረግ ወይም በሰዎች መካከል ጠንካራ ጠብ እንዲፈጠር ማድረግ ማለት ነው፡፡

እንደማያቋርጥ ነጠብጣብ

ይህ የሚያስተላልፈው መልእክት በማያቋርጥ ሁኔታ የሚንጠባጠብ ዝናብ ነው የሚል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የማቋርጥ የዝናብ ነጠብጣብ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የዝናብ ቀን

“የማያቋርጥ ዝናብ የሚዘንብበት ቀን”

እሷን ማቆም ንፋስን እንደማቆም ወይም ዘይትን በቀኝ እጅህ ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው፡

የዚህ መልእክት እርስዋን ለማስቆም መሞከር ነፋስን እንደ ማቆም ወይም በእጅህ ዘይትን እንደ መጨበጥ በጣም አስቸጋሪና ጥቅም አልባ ነው፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እርስዋን ማስቆም

“እርስዋን ወደኋላ መመለስ” ወይም “እርስዋን መቆጣጠር፡፡” የዚህ መልእክት እርስዋን ከመጣላት ለማስቆም መሞከር የሚል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርስዋን ከመጣላት ማስቆም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ንፋስን ማስቆም

“ነፋስን መመለስ” ወይም “ነፈስን በቁጥጥር ስር ማዋል”