am_tn/pro/27/13.md

2.4 KiB

ለማይታወቅ ሰው ብድር በዋስትና ገንዘብ ያስያዘውን ሰው ልብስ ውሰድበት

ገንዘብ በማበደር ጊዜ አበዳሪ ከተበዳሪው ብድሩን መልሶ ለመክፈሉ እንደ ዋስትና የሚሆን ልብስ ወይም ሌላ ነገር ይወስዳል፡፡ ገንዘቡ ከተመለሰለት በኋላ የያዘውን መያዣ ይመልሳል፡፡ ተበዳሪው በጣም ድኃ ከሆነ ሌላ ሰው ስለ እርሱ እንደ ዋስትና ለአበዳሪው የሆነ ነገር ይሰጣል፡፡ ይህንን በምሳሌ 20:16 እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የማይታወቅ ሰው የተበደረው ብድር ተመልሶ እንዲከፈል ተያዥ ከሆነው ሰው እንደ ዋስትና እንዲሆን ልብስ ውሰድበት” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በዋስትና ገንዘብ ያስያዘውን ሰው

የተበደረው ብድር እንደገና ለመከፈሉ እንደ ዋስትና እንዲሆን አንድ ሰው አንድ ነገር ለአበዳሪው ይሰጣል ማለት ነው፡፡ ይህንን በምሳሌ 20:16 እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተበደረው ብድር ተመልሶ እንዲከፈል ተያዥ የሆነው ሰው” ወይም “ብድርን ለመክፈል ቃል የገባው ሰው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

መያዣ ውሰድበት

“አነድን ነገር በመያዣነት መውሰድ” ዕዳውን እንዲከፍል አንድ ሰው እንደ መያዣ ወይም ቃል ኪዳን የሰጠውን ነገር መያዝ ማለት ነው፡፡ ይህንን በምሳሌ 20:16 እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ብድሩ ለመከፈሉ እንደ ዋስትና ልብሱን ውሰድበት” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ጎረቤቱን የሚባርክ ሰው

“አንድ ሰው ለጎረቤቱ በረከት ቢሰጠው”

ባርኮቱ እንደ እርግማን ይቆጠራል

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጎረቤቱ በረከቱን እንደ እርግማን ይቆጥረዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)