am_tn/pro/27/05.md

1.9 KiB

የተገለጠ ተግሳጽ ይሻላል

ይህ “ተግሳጽ” የሚለው ረቂቅ ስም “መገሰጽ” በሚለው ግስ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በገልጽ መገሰጽ ይሻላል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ከተሰወረ ፍቅር

“በግልጽ ከማይታይ ፍቅር ይልቅ፡፡” ይህ “”ፍቅር” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ የግስ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በምስጢር ከመወደድ ይልቅ” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የጓደኛ ማቁሰል የታመኑ ናቸው

“ጓደኛ የሚያመጣው ጉዳቶች የታመኑ ናቸወ፡፡” እዚህ ላይ “ቁስል” የሚለው ቃል ጓደኛ ሲገስጸውና ሲያስተካክለው ሰውየው የሚሰማው ሕመምና ሀዘንን ይወክላል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የጓደኛ ማቁሰል የታመኑ ናቸው

የጓደኛ ተግሳጽ ታማኝነት ተግሳጹ የሚያመጣው ሀዘን ታማኝ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምንም እንኳ ሀዘን ቢያስከትልም፣ የጓደኛ ተግሳጽ የታመነ ነው” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ጠላት ግን ከመጠን በላይ ይስማል

የጠላት መሳም ታማኝ እንዳልሆነ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን የጠላት ብዙ መሳም ታማኝ አይደሉም” ወይም “ነገር ግን ጠላት ከመጠን በላይ በመሳም ሊያታልልህ ይሞክር ይሆናል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ

ከመጠን በላይ

“በብዛት” ወይም “ብዙ ጊዜ”