am_tn/pro/27/03.md

2.3 KiB

የሞኝ ሰው ትንኮሳ ግን ከሁለቱም እጅግ የከበደ ነው

ሞኝ ሰው ሲተነኩሰህ የሚገጥምህ ትዕግስተኛ የመሆን ችግር ያ ችግር እጅግ የከበደ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሞኝ ትንኮሳ መታገስ ከሁለቱም ይከብዳል” ወይም “ሞኝ ሲተነኩስህ መታገስ እነርሱን ለመሸከም ከመታገስ የበለጠ ይከብዳል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሞኝ ትንኮሳ

“በሞኝ አማካኝነት የሚመጣ ችግር፡፡” “ትንኮሳ” ቁጣ ወይም መራራነት የሚፈጥሩ ድርጊቶች ወይም ቃላት ናቸው፡፡

የንዴት ጭካኔና የቁጣ ጎርፍ አለ፣ በቅናት ፊት መቆም የሚችል ግን ማን ነው?

“ንዴት፣” “ጭካኔ” እና “ቁጣ” እንደ ቅጽል ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ተናዳጅ ሰው ጨካኝ ነው፣ ቁጡ ሰው ይጎዳል፣ ነገር ግን በቀናተኛ ሰው ፊት ማን መቆም ይችላል? (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ጭካኔ

“ሀይለኛነት”

የቁጣ ጎርፍ

“የቁጣ አጥፊነት፡፡” እዚህ ላይ ቁጣ ሀይለኛ ጎርፍ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በቅናት ፊት መቆም የሚችል ግን ማን ነው?

ይህ ጥያቄ ማንም ሰው በቅናት ፊት መቆም እንደማይችል የሚያመለክት ነው፡፡ እንደ ዓረፈተ-ሃሳብ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን በቅናት ፊት መቆም የሚችል ማንም ሰው የለም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በቅናት ፊት መቆም

እዚህ ላይ መቆም የሚለው ቃል ጥቃት በሚፈጽም ቀናተኛ ሰው ላለመጎዳት ጠንካራ እና ጽኑ መሆንን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቀናተኛ ሰውን መከላከል” ወይም “ቀናተኛ ሰው ጥቃት ሲፈጽምበት በጥንካሬ መጽናት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)