1.8 KiB
1.8 KiB
ነገ በሚሆነው አትመካ
ይህ ነገ ይሆናል ብለህ ስለምትጠብቀው ነገር ጉራ እንደትነዛ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ ይህ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለነገ ስላለህ እቅድ በኩራት አትናገር” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ቀኑ የሚያመጣውን
በተወሰነ ቀን የሚከናወነው ነገር ያንን ክስተት ቀኑ እንደሚያመጣው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በዚያ ቀን የሚሆነውን” ወይም “ነገ የሚሆነውን” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
በራስህ አፍ ሳይሆን … የራስህ ከንፈሮች ሳይሆኑ
“ያመስግኑህ” የሚለውን ቃል ከመጀመርያው ሀረግ በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ ቃላቶቹ ሊደጋገሙ ይችላሉ፡፡ እዚህ ለላይ ሰውየው በ “አፉ” እና በ “ከንፈሮቹ” ተወክሏል ምክንያቱም እነዚህ ለመናገር የሚጠቅሙ የሰውነት አካላት ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የራስህ አፍ አያመስግንህ … የራስህ ከንፈሮች አያመስግኑህ” ወይም “ራስህን አታመስግን … ራስህን አታመስግን” (አስጨምሬ እና ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)
የማያውቅህ ሰው
“ያመስግኑህ” የሚለውን ቃል ከመጀመርያው ሀረግ በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ እዚህ ላየ ቃላቶቹ ሊደጋገሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የማያውቅህ ሰው ያመስግንህ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)