am_tn/pro/26/27.md

2.5 KiB

ጉድጓድን የሚቆፍር ሰው እርሱ ይገባበታል

ይህ ሰው ጉድጓድ የሚቆፍረው ሌላ ሰው በዚያ ጉድጓድ ላይ እንዲወድቅበት እንደ ወጥመድ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሌላ ሰው ለማጥመድ ጉድጓድን የሚቆፍር ማንኛውም ሰው እርሱ ይገባበታል” ወይም ““ሌላ ሰው ለማጥመድ በማሰብ አንድ ሰው ጉድጓድ ከቆፈረ፣ የቆፈረው ሰው ራሱ ይገባበታል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ድንጋይንም የሚያንከባልል ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል

ይህ ሰው በኮረብታ ላይ ሆኖ ወደታች ትልቅ ድንጋይን የሚያንከባልለው ከታች ያለውን ሌላ ሰው ለመጨፍለቅ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው ከታች ያለውን ሌላ ሰው ለመጨፍለቅ በኮረብታ ላይ ሆኖ ወደታች ትልቅ ድንጋይ የሚያንከባልል ከሆነ፣ ድንጋዩ በራሱ ላይ ተመልሶ ይንከባለልበታል” ወይም “አንድ ሰው ሌላ ሰው ለመጉዳት ድንጋይ የሚያንከባልል ከሆነ ድንጋዩ ተመልሶ ራሱን ይጨፈልቀዋል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ውሸታም ምላስ የጎዳቸውን ሰዎች ይጠላል

“ውሸታም ምላስ” የሚለው ሀረግ ውሸት የሚናገረውን ሰው ይወክላል፡፡ ሰዎችን መጉዳት በሰዎች ላይ ችግር መፍጠርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ውሸታም ሰው በውሸቱ የጎዳቸውን ሰዎች ይጠላል” (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሸንጋይ አፍም ጥፋትን ያመጣል

“ሸንጋይ አፍ” የሚለው ሀረግ ሰዎችን የሚሸነግለውን ሰው ይወክላል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- ሌሎችን የሚሸነግል ሰው ችግር ይፈጥራል፡፡ ወይም 2) ሌሎችን የሚሸነግል ሰው ያጠፋቸዋል (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

መሸንገል

አንድን ሰው እውነተኛነት በሌለው ሁኔታ ማመስገን፣ ወይም አንድን ሰው እውነተኛ ላልሆኑ ነገሮች ማመስገን