am_tn/pro/26/24.md

3.3 KiB

ስሜቱን በከንፈሮቹ ይሸነግላል

ስሜትን መሸንገል ስሜቱን ሰዎች እንዳያውቁ መደበቅን ይወክላል፡፡ “ከንፈሮቹ” የሚለው ቃል ለተናገረው ንግግር ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሚናገረው ንግግር ስሜቱን ይደብቃል” ወይም “እውነተኛ ስሜቱን ሰዎች ሊያውቁ በማይችሉበት ሁኔታ ይናገራል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ተንኮሉን ግን በውስጡ ያኖራል

ተንኮለኛ መሆን ሰውየው ተንኮል በውስጡ ያጠራቅም እንደነበር ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- “ተንኮል” ውሸትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ብዙ ውሸቱን ይወድደዋል” 2) ተንኮል ሰዎችን ለመጉዳት ምስጢራዊ እቅዶችን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎችን ለመጉዳት በምስጢር አቅዷል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን አትመነው

“ነገር ግን የሚናገረውን አትመነው”

በልቡ ውስጥ ሰባት ርኩሰቶች አሉ

ሰባት ቁጥር ፍጹምነትን ይወክላል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ርኩሰት” እግዚአብሔር የሚጠላውን አመለካከት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ልቡ ሙሉ በሙሉ በጥላቻ ነገሮች የተሞላ ነው” ወይም 2) “ርኩሰት” ለሰዎች ያለውን ጥላቻ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ““ልቡ ሙሉ በሙሉ በጥላቻ የተሞላ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ምንም እንኳ ጥላቻው በሽንገላ የተሸፈነ ቢሆንም

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምንም እንኳ ሽንገላው ጥላቻውን ቢሸፍነውም” ወይም “ምንም እንኳ ጥላቻውን በሽንገላው ቢሸፍነውም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ምንም እንኳ ጥላቻው በሽንገላ የተሸፈነ ቢሆንም

ሰዎች እነርሱን እንደሚጠላቸው እንዳያውቁ መደበቁ ጥላቸውን እንደሸፈነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምንም እንኳ ሰዎች እነርሱን እንደሚጠላቸው እንዳያውቁ ለመደበቅ ቢዋሽም” ወይም “ምንም እንኳ ሰዎች እነርሱን እንደሚጠላቸው እንዳያውቁ ቢዋሽም” “Though he lies so that people will not know that he hates them” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፋቱ ግን በጉባኤ ይገለጣል

መገለጥ መለየት ወይም መታወቅ የሚለውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፋቱ በጉባኤ ይታወቅበታል” ወይም “ጉባኤው ክፋቱን ይደርስበታል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ጉባኤው

“የእስራኤል ማህበረሰብ”