am_tn/pro/26/22.md

3.3 KiB

የሐሜት ቃላቶች እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው

ለመብላት ጣፋጭ እንደሆነ ምግብ ሐሜትም ለመስማት ደስ የሚያሰኝ ሰለመሆኑ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሐሜት ቃላቶች ለመስማት ደስ የሚያሰኙ ናቸው” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎችም ይወርዳሉ

ይህ ሐሜት የሚናገራቸው ቃላቶች ወደ ሰው አእምሮ ገብተው ሃሳቡን እንደሚያበላሹ የሚናገር ሲሆን ወደ ሆዱ እንደሚገባ ምግብ ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ ይህ ዓረፍተ-ሃሳብ በምሳሌ 18:8 ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ሰው አእምሮ ይገቡና ሃሳቡን ያበላሻሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንሚያቃጥሉ ከንፈሮችና እንደ ክፉ ልብ በብር ፈሳሽ የተለበጠ የሸክላ ድስት እንዲሁ ነው

ይህ ተነፃፃሪ ዘይቤ ክፋትን በልባቸው ለመደበቅ የተለያዩ ነገሮችን የሚናገሩ ሰዎች ጥሩ እንዲመስል ለማድረግ በብር ፈሳሽ እንደተለበጠ የሸክላ ድስት ነው፡፡ እነዚህ ሀረጎች ቅደም ተከተላቸው ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚያቃጥሉ ከንፈሮች ያላቸው ሰዎችና ክፉ ልብ በብር ፈሳሽ እንደተለበጠ የሸክላ ድስት ነው፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በብር ፈሳሽ የተለበጠ የሸክላ ድስት

“የሸክላ ድስትን የሚሸፍን የሚያብረቀርቅ ቅብ፡፡” የሸክላ ድስት ርካሽና በሁሉም ስፍራ የሚገኝ ነው፡፡ ስለዚህ የሚያብረቀርቅ እንዲሆንና በጣም ውድ እንደሆነ ለማስመሰል ሰዎች በሚያብረቀርቅ ቅብ ይሸፍኑታል፡፡

የሚያቃጥሉ ከንፈሮችና ክፉ ልብ እንደዚሁ ናቸው

ይህ የሚወክለው የሚያቃጥሉ ከንፈሮችና ክፉ ልብ ያለውን ሰው ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚያቃጥሉ ከንፈሮችና ክፉ ልብ ያለው ሰው እንደዚሁ ነው” ወይም “መልካም ንግግር የሚናገር ነገር ግን ልቡ ክፉ የሆነ ሰው እንደዚሁ ነው” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚያቃጥሉ ከንፈሮች

“የሚያቃጥሉ” የሚለው ቃል “ከመጠን ያለፈ ስሜታዊ መሆን” ለማመልከት ተለዋጭ ዘይቤ ሲሆን “ከንፈሮች” የሚለው ቃል ደግሞ “ንግግር” ለማመልከት ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስሜታዊ ንግግር” ወይም “ጥሩ ነገሮች መናገር” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉ ልብ

ልብ የሰውን ሃሳብ፣ ዝንባሌ፣ ፍላጎት ወይም ስሜት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሃሳብ” ወይም “ክፉ ምኞት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)