am_tn/pro/26/09.md

1.2 KiB

እንደ እሾህ … በሞኝ አፍ ውስጥ ያለ ምሳሌ እንዲሁ ነው

ሁለቱ እንዴት ተመሳሳይነት እንዳላቸው በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሰካራም እጅ እንደገባ እሾህ በሞኝ አፍ ውስጥ ያለ ምሳሌ አደገኛ ነው” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰካራም እጅ እንደገባ እሾህ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ሰካራም እሾህ ያለው ቁጠቋጦ በእጁ ከያዘ፣ እሾሁ እጁን ይወጋዋል፣ ወይም 2) ሰካራም ሰው ከተቆጣ፣ እሾህ ያለው ቁጠቋጦ ይዞ በሰዎች ላይ ይጥለዋል፡፡ ለሁለተኛው ትርጉም “እሾህ” የሚለው ቃል የእሾህ ቁጥቋጦን ይወክላል፡፡ (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

በሞኞች አፍ

እዚህ ላይ “አፍ” ለመናገር ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሞኞች ንግግር” ወይም “ሞኞች የተናገሩት ነገር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ሞኝ ይቀጥራል

“ለሞኝ ስራ ይሰጣል”