am_tn/pro/26/07.md

1.5 KiB

እንደ እግሮች … በሞኝ አፍ ያለ ምሳሌ እንዲሁ ነው

የእነዚህ ሀረጎች አቀማመጥ ቅደም ተከተሉ ሊለወጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሞኝ አፍ ያለ ምሳሌ እንደ ተንጠለጠሉ የሰለሉ የሽባ እግሮች ናቸው” ወይም “በሞኝ አፍ ያለ ምሳሌ እንደ ተንጠለጠሉ የሰለሉ የሽባ እግሮች የማይጠቅሙ ናቸው” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሽባ

መንቀሳቀስ የማይችል ሰው ወይም ሁሉም ወይም ከፊል ሰውነቱ እንዲህ የሚሰማው

በሞኞች አፍ

“አፍ” ለመናገር ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሞኞች ንግግር” ወይም “ሞኞች የሚናገሩት ነገር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ድንጋይን በወንጭፍ ማሰር

ወደ ረጅም ርቀት ድንጋይ ለመወርወር ሰዎች ድንጋይ በወንጭፍ ያስቀምጣሉ ከዚያም ግንጋዩ በጣም በፍጥነት ወደቦታው እንዲስፈነጠር ወንጭፉን ያዞሩታል፡፡ ድንጋይን በወንጭፍ የማሰር ውጤት በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዳይወረወር ድንጋይን በወንጭፍ ማሰር” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለሞኝ ክብር መስጠት

“ሞኝን ማክበር”