am_tn/pro/26/05.md

1.8 KiB

ሞኝን እንደ ሞኝነቱ መልስለት፣ በሞኝነቱም ተባበረው፣

ለሞኝ ስትመልስለት በሞኝነቱ መተባበር በሞኝነት መንገድ ለእርሱ መመለስን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሞኝ እንደሞኝነቱ መልስለት” ወይም “ለሞኝ በሞኝነት መልስለት”

ስለዚህ በዓይኖቹ ጥበበኛ የሆነ እንዳይመስለው

ዓይን መመልከትን ይወክላል፣ መመልከት ደግሞ ሃሳብንና ግንዛቤን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለዚህ በእርሱ ግንዛቤ ጥበበኛ የሆነ እንዳይመስለው” ወይም “ስለዚህ ራሱን ጥበበኛ እንደሆነ እንደያስብ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በሞኝ ሰው እጅ መልዕክትን የሚልክ ሁሉ

እዚህ ላይ እጅ መልእክትን ለማድረስ ሞኝ ያለውን ኃላፊነት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መልእክት እንዲያደርስለት ሞኝን የሚልክ ሀሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የራሱን እግር ይቆርጣል

የራስን እግር መቁረጥ ራስን ለመጉዳት የግነት መግለጫ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የራሱን እግር እንሚቆርጥና ሁከትን እንደሚጠጣ ሰው ራሱን ይጎዳል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ግነት እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሁከትንም ይጠጣል

ሁከት አንድ ሰው ሊጠጣው የሚችል መርዛም ፈሳሽ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሁከት ፈጣሪነት ራሱን ይጎዳል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)