am_tn/pro/26/01.md

1.3 KiB

በበጋ ጊዜ እንደሚወርድ በረዶና በመከር ጊዜ እንደሚዘንብ ዝናብ

ብዙውን ጊዜ በረዶ በበጋ ጊዜ አይወርድም፣ ዝናብ ደግሞ በመከር ጊዜ አይዘንብም፡፡ ይህ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በረዶ በበጋ ጊዜ መውረድና ዝናብ ደግሞ በመከር ጊዜ መዝነብ እንግዳ ነገር እንደሆነ ሁሉ” (ተነፃፃሪ ዘይቤ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ያልተገባ እርግማን ማንም ላይ አይደርስም

ሰውን የማይጎዳ እርግማን መሬት ላይ እንደማታርፍ ወፍ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለዚህ ያልተገባ እርግማን በታሰበው ሰው ላይ አይደርስም” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያልተገባ እርግማን

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በማይገባው ሰው ላይ የሚደረግ እርግማን” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

አረፈ

በአንድ ሰው ወይም ነገር ላይ ማረፍ