am_tn/pro/25/25.md

1.8 KiB

ለተጠማ ሰው ቀዝቃዛ ውሃ እንደሚያረካው ሁሉ፣ ከሩቅ አገር የመጣ የምስራችም እንዲሁ ነው

ቀዝቃዛ ውሃ ከሚያድስና ከሚያስደስት መልካም የምስራች ጋር ተነጻጽሯል፡:፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በክፉ ሰዎች ፊት የሚንበረከክ ጻድቅ ሰው፣ እንደ ተበከለ ወንዝና እንደተበላሸ ምንጭ ነው

አንድ ሰው ጻድቅ ለሚያምነት ነገር በጽናት እንዲቆም እንደሚጠብቅ ሁሉ እንዲሁ፣ አንድ ሰው ወንዝና ምንጭ ንጹህ ውኃ እንዲኖረው ይጠብቃል፡፡ የተበከለ ወንዝና የተበላሸ ምንጭ በአቋሙ ከወደቀ ጻድቅ ሰው ጋር ተነጻጽሯል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በክፉ ሰዎች ፊት የሚንበረከክ

መንበርከክ ለሚከተሉት ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡- 1) ክፉ ሰዎችን ለመጋፈጥ አለመፈለግ ወይም 2) በክፋታቸው መሳተፍ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎች ክፋት እንዲያደርጉ መፍቀድ” ወይም “ክፉ ሰዎች የሚሰሩትን ስራ መስራት የሚጀምር ሰው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መንበርከክ

መንበርከክ መልካም ስራ መስራት መቀጠል ለአለመቻል ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለመቆም አለመቻል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በክፉ ሰዎች ፊት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ክፉ ሰዎች ሲያጠቁት” ወይም 2) “ክፉ ሰዎች ክፉ ነገር እንዲሰሩ ሲገፉት፡፡” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)