am_tn/pro/25/23.md

1.5 KiB

የሰሜን ነፋስ

በእስራኤል አገር ከሰሜን የሚመጣ ነፋስ ብዙ ጊዜ ዝናብ ይዞ ይመጣል፡፡ ተርጓሚዎች ተመሳሳይ ውጤት ለሚያሳይ ሀኔታ የተለያዩ ዓይነት ነፋሳትን ለመጠቀም ነጻነት አላቸው፣ ለምሳሌ፡- “ቀዝቃዛ ነፋስ፡፡”

ምስጢር የሚያባክን ምላስ

አንዳንድ ትርጉሞቸ ይህን “ምስጢር የሚያባክን አንድ ሰው” ብለው ተርጉመውታል፡፡

የሰዎችን ፊት ያስቆጣል

ፊት ለሰውየው ተዛምዶአዊ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሌሎች ሰዎችን በጣም ያስቀጣል፣ ይህንን ደግሞ በፊታቸው ማየት ትችላላህ” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

በጣራ ማእዘን

በዚያን ጊዜ የነበሩ ቤቶች ለጥ ያለ ጣራ ነበራቸው፡፡ የጥንት እስራኤላውያን ጣራቸውን ለመስራት ብዙ ጊዜ ይወስድባቸው ነበር፡፡ ጣራው ከቤቱ ውስጠኛው ክፍል ይልቅ ቀዝቃዛ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ለመኝታ የሚሆን ትልቅ መጠለያ በጣራው በአንዱ ማእዘን ላይ ይሰሩ ነበር፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ጠበኛ ሚስት

“ብዙ ጊዜ የምትጨቃጨቅና የምታማርር ሚስት”