am_tn/pro/25/13.md

2.0 KiB

በምርት መሰብሰቢያ ወቅት እንዳለ የበረዶ ቅዝቃዜ ታማኝ መልዕክተኛ

እዚህ ላይ ታማኝ መልእክተኛ ከበረዶ ቅዝቃዜ ጋር ተነጻጽሯል ምክንያቱም ሁለቱም ደስ የሚያሰኙ ናቸው፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የበረዶ ቅዝቃዜ

በረዶ የሚወርደው መተራራ ጫፎች ላይ ብቻ ነው፣ ምርት የሚሰበሰበው ደግሞ በሞቃት ወቅት የአየር ሁኔታ ነው፣ ስለዚህ ይህ ምናልባት ከንጹህ ምንጭ ለሚወጣ ቀዝቃዛ ውኃ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በረዶ

እንደ ዝናብ ከሰማይ የሚወርድ ነጭ የደቀቀ በረዶ

የጌቶቹን ሕይወት ይመልሳል

ደካማና አቅመ ቢስ የሆኑትን ጌቶቹን ጠንካራና በእረፍት የተሞሉ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡

የማይሰጠውን ስጦታ እሰጣለሁ ብሎ የሚመካ ሰው ዝናብ እንደሌለው ደመናና ንፋስ ነው

ብዙ ትርጉሞች ይህን ተለዋጭ ዘይቤ እንደ ተነፃፃሪ ዘይቤ ተርጉመውታል፣ የሀረጎቹንም ቅደም ተከተል ለውጠዋቸዋል፡፡ ዝናብ ለእስራኤላውያን በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የሚዘንበው በጣም ትንሽ ዝናብ ነው፣ ስለዚህ ዝናብ የሌለው ደመና ጥቅም የሌለውና እስራኤላውያንን የሚያሳዝን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚመካ ነገር ግን የማይሰጥ ሰው ዝናብ እንደሌለው ደመናና ነፋስ ነው” ወይም “የማይሰጥ ነገር ግን የሚመካ ሰው ዝናብ እንደሌለው ደመናና ነፋስ ጥቅም የሌለውና ኀዘን የሚያመጣ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)