am_tn/pro/25/11.md

2.7 KiB

በብር ላይ እንደተቀረጸ የወርቅ ንድፍ፣ በትክክለኛ ሁኔታ የተነገረ ቃል እንዲሁ ነው

“በትክክለኛ ሁኔታ የተነገረ ቃል” መልካምነት በአካል እንደሚታይ “በብር ላይ እንደተቀረጸ የወርቅ ንድፍ” ውበት ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ብዙ ትርጉሞች ይህንን ተለዋጭ ዘይቤ እንደ ተነፃፃሪ ዘይቤ በመተርጎም የሀረጎቹን ቅደም ተከተል ለውጠዋቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በትክክለኛ ሁኔታ የተነገረ ቃል፣ በብር ላይ እንደተቀረጸ የወርቅ ንድፍ ውብ ናቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በብር ላይ እንደተቀረጸ የወርቅ ንድፍ

የጥንት እስራኤላውያን ዛሬ ብዙ ሰዎች የሚያውቁትን ንድፍ አያውቁም፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ንድፎች” የሚለው “ዲዛይን” ተብሎ ሊተረጎም ይገባል፡፡” አማራጭ ትርጉም፡- “የወርቅ ዲዛይን በብር ሳህን ላይ የተቀረጸ” ወይም 2) “ፖም” አንድ ሰው በዝርግ ወይም በጎድጓዳ ሳህን ላይ ያስቀመጠው ወርቃማ ቀለም ያለው ሌላ ዓይነት ፍሬ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በብር ሳሳን ላይ የተቀመጠ ወርቃማ ቀለም ያለው ፍሬ”

የተነገረ ቃል ነው

ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው የተናገረው መልእክት ነው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ለሚሰማ ጆሮ የጥበበኛ ተግሳጽ እንደ ወርቅ ቀለበት፣ ከንጹህ ወርቅም እንደተሰራ ጌጥ ነው

“የጥበበኛ ተግሳጽ” ዋጋና አስፈላጊነት የወርቅ ውበትና ዋጋ እንዳለው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ብዙ ትርጉሞች ይህንን ተለዋጭ ዘይቤእንደ ተነፃፃሪ ዘይቤ ተርጉመውታል እና የሀረጎቹ ቅደም ተከተል ቀይረውታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የጥበበኛ ተግሳጽ ለሚሰማ ጆሮ እንደ ወርቅ ቀለበት ወይም የወርቅ ጌጥ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለሚሰማ ጆሮ

ጆሮ ለሰው ሁለንተና ተዛምዶአዊ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለመስማት ፈቃደኛ የሆነ ሰው” (ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)