am_tn/pro/24/32.md

1.3 KiB

ተግሳጽን ተቀበልሁ

“ትምህርት ተማርሁ”

ጥቂት እንቅልፍ … ጥቂት ለማረፍ … ድህነት ይመጣል

የተዘለሉትን ቃላት መሙላት ያስፈልግህ ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለራስህ እንዲህ ትለው ይሆናል፣ ‘ጥቂት እንቅልፍ … ጥቂት ማረፍ’ - ነገር ግን ወዲያውኑ ድህነት ይመጣል” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ድህነት በአንተ ላይ ይመጣል

አንዳንድ ትርጉሞች እንዲህ ብለው ተርጉመውታል፣ “ድህነት እንደ ሌባ በአንተ ላይ ይመጣል፡፡” ድህነት ሰነፍ ሰውን ሊያጠቃ የሚችል ሰው ወይም እንስሳ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ችግርህም መሳርያ እንደታጠቀ ወታደር ይመጣብሃል

ችግር ሰነፍ ሰው ሊያጠቃ የሚችል ሰው እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ችግርህም መሳርያ እንደታጠቀ ወታደር ሆኖ ወደ አንተ ይመጣብሃል” (ተነፃፃሪ ዘይቤ እና ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)