1.6 KiB
1.6 KiB
ወንጀለኛውን … የሚለው በሕዝብ ዘንድ ይረገማል፣ በመንግስታትም ዘንድ ይጠላል፡፡
“መንግስታት” የሚለው ቃል በአገሮቹ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ምትክ ስም ነው፡፡ እነዚህ ቃላት በገቢር ቅርጽ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉውን ሰው … ለሚለው ሰዎች ይረግሙታል፣ የሌሎች አገሮች ሕዝቦች ደግሞ ይጠሉታል”
ክፉ ሰው … ጻድቅ ሰው
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ሰዎች ለክፉ ሰው ጻድቅ ሰው ብለው ሊጠሩት በፍጹም አይገባም ወይም 2) ሕግ በመተላላፉ ምክንያት ወንጀለኛ ለሆነ ሰው ማም ሰው ንጹሕ ነው ሊለው አይገባም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕግ በመተላላፉ ምክንያት ወንጀለኛ የሆነ ሰው … ንጹሕ ሰው”
ደስ ይለዋል
“በጣም ደስተኛ ይሆናል”
የደግነት ስጦታዎችም ወደ እነርሱ ይመጣሉ
ስጦታዎች በራሳቸው መንቀሳቀስ የሚችሉ ሰዎች እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ “ደግነት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ጥሩ ስጦታዎች ይሰጧቸዋል” (ሰውኛ ዘይቤ እና ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
የደግነት ስጦዎች
“ጥሩ ነገሮች” ወይም “በረከቶች”