am_tn/pro/24/15.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እነዚህ ጥቅሶች “ሰላሳ የተግሳጽና የእውቀት ቃሎች” የተባሉትን ይቀጥላሉ (ምሳሌ 22:20)፡፡

አድፍጠህ አትጠብቅ

“አድፍጠህ አትጠብቅ” የሚሉት ቃላት ፈሊጥ ነው፡፡ “አድፍጠህ አትጠብቅ” የሚለውን በምሳሌ 1፡11 ላይ እንደተረጎምኸው ተርጉመው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አጋጣሚውን ለመጠቀም አድፍጠህ አትጠብቅ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤቱ

የጻድቅ ሰው ቤት

እንደገና ይነሳል

“በእግሩ እንደገና ይነሳል” ወይም “እንደገና ይቆማል”

ክፉ ሰዎች ግን በመቅሰፍት ላይ ይወድቃሉ

ጸሐፊው “መቅሰፍት” በሌሎች ሰዎች ላይ መጥፎ ነገሮችን የሚያደርግ ሰው እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ እነዚህ ቃላት እንደ ገቢር ቅርጽ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ክፉ ሰዎችን ለመጣል መቅሰፍት ይጠቀማል” (ሰውኛ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ይወድቃሉ

ይህ ተለዋጭ ዘይቤ ሲሆን የሚወክለው ቆሞ የነበረ ሰው ነገር ግን ሌላ ሰው ወደ መሬት ወደታች ጎትቶ ያመጣው ወይም እንዲወድቅ ያደረገው ሰው ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መቅሰፍት

በሰዎችና በንብረታቸው ላይ መጥፎ ነገር የተከናወነበት ጊዜ