1.4 KiB
1.4 KiB
አጠቃላይ መረጃ፡-
እነዚህ ጥቅሶች “ሰላሳ የተግሳጽና የእውቀት ቃሎች” የተባሉትን ይቀጥላሉ (ምሳሌ 22:20)፡፡
ተዋጊና ጥበበኛ
ይህ “ጥበብ” የሚለው ረቂቅ ስም “ጥበበኛ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበበኛ ተዋጊ” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
እውቀት ያለው ሰው ጥንካሬውን ይጨምራል
ይህ “እውቀት” እና “ጥንካሬ” የሚሉት ረቂቅ ስሞች “እወቅ” በሚለው ግስ እና “ጠንካራ” በሚለው ቅጽል ሊተረጎም ይችላል” አማራጭ ትርጉም፡- “ብዙ ነገሮች የሚያውቅ ሰው ጠንካራ ነው ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ያውቃል” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
በጥበበኛ ምክር
ይህ “ምክር” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግስ ሊተረገም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምን ማድረግ እንዳለብህ የሚነግሩህ ጥበበኛ ሰዎች” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
ጦርነትህን መዋጋት ትችላለህ፣
“ጦርነት ተዋጋ”
አማካሪዎች
ለመንግስት አካላት ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚነግሩአቸው ሰዎች