am_tn/pro/24/03.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እነዚህ ጥቅሶች “ሰላሳ የተግሳጽና የእውቀት ቃሎች” የተባሉትን ይቀጥላሉ (ምሳሌ 22:20)፡፡

ቤት በጥበብ ይሰራል፣

“ጥበብ” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ እነዚህ ቃላቶች በገቢር ግስ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ጥሩ ቤት መስራት የሚፈልጉ ከሆነ ጥበበኛ መሆን አለባቸው” (ረቂቅ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በማስተዋልም ይጸናል

ይህ “ማስተዋል” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ቤት ለመስራት የሚፈልጉ ከሆነ መልካም ባህርይና መጥፎ ባህርይ ምን እንደሆነ መረዳት አለባቸው” (ረቂቅ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ይጸናል

“ይጸናል” የሚለው ቃል ጽኑ እና ጠንካራ መሆን ማለት ነው፡፡ “ቤት” የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩት ቤተሰቦች ምትክ ስም ነው፣ ጽኑ እና ጠንካራ ሆኖ የተሰራው ቤት ደግሞ በቤት ውስጥ ለሚኖሩት ቤተሰቦች ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በእውቀትም ክፍሎቹ ይሞላሉ

“እውቀት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች መኖርያ ክፍሎቻቸው እንዲሞሉ የሚፈልጉ ከሆነ ውድና አስደሳች የሆነውን ነገር ማወቅ ያስፈልጋቸዋል” (ረቂቅ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)