am_tn/pro/22/17.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ቁጥር 17 ለመጽሐፈ ምሳሌ አዲስ ክፍል መግቢያ ሆኖ ይጀምራል፡፡

ጆሮህን አዘንብልና አድምጥ

እዚህ ላይ “ጆሮ” የሚለው ቃል የሚያደምጠውን ሰው ይወክላል፡፡ ጸሐፊው አንድን ሰው በጥሞና ስለማድመጥ ሲናገር ጆሮ ወደተናጋሪው መጠጋት እንዲችል በሚናገረው ሰው ላይ እንደመደገፍ አድርጎ ገልጾታል፡፡ “ጆሮን ማዘንበል” የሚለውን በምሳሌ 4፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትኩረት በመስጠት አድምጥ” ወይም “በትኩረት አድምጥ” (ተዛምዶአዊ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የጥበበኛ ቃላት

“ጥበበኛ ሰዎች የሚናገሩት”

ልብ በል

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሚገባ ለመረዳትና ለማስታወስ የምትችለውን ሁሉ አድርግ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እውቀቴ

የሚናገረው ሰው ምናልባት በምሳሌ 1፡8 ላይ ካለው አባት ጋር ተመሳሳይ ሊሆን ይችላሉ፡፡ “አውቀቴ” በማለት የሚናገረው ስለ “ጥበበኛ ቃላት” ሊሆን ይችላል፡፡ “እውቀት” የሚለው ረቂቅ ስም “እወቅ” በሚለው ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከአንተ ጋር የምካፈለው እኔ ያለኝ እውቀት” ወይም “የማውቀውን” (የስም ቅፅሎች የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ ዝግጁ ናቸው

ለመናገር ዝግጁ የሆነው ሰው ለመነገር ዝግጁ እንደሆኑት ቃላት ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ በማንኛውም ጊዜ ቃላቶቹን ለመናገር ትችላለህ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ዛሬ ለአንተ

“ዛሬ፡፡ አዎ፣ እኔ እያስተማርኩህ ነው፣” ተናጋሪው የሚያስተምረው አድማጩን እንጂ ሌላ ሰውን እያስተማረ እንዳልሆነ አጽንዖት ይሰጣል፣ አድማጩን የሚያስተምረው ደግሞ አድማጩ መማር ስለሚያስፈልገው ነው፡፡ በዚህ መንገድ አጽንዖት መስጠት በቋንቋህ ተስማሚ ካልሆነ በሌላ መንገድ አጽንዖት ልትሰጠው ትችላህ ወይም “ለአንተ” የሚለውን ቃል ሳትተረጉመው ልታልፈው ትችላለህ፡፡