am_tn/pro/22/09.md

1.6 KiB

ቸር አይኖች ያሉት ሰው ይባረካል

እነዚህ ቃላት በገቢር ቅርጽ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቸር ዓይን ያለውን ሰው እግዚአብሔር ይባርከዋል፡፡ (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ቸር አይኖች ያሉት ሰው

ዓይን ሌሎች ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ለማየት ምትክ ስም ነው፣ “ቸር ዓይን” ደግሞ ማየት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሌሎች ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ይሰጣል፡፡ ዓይን ለሰው ሁለንተና ተዛምዶአዊ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቸር ሰው” ወይም “ለሌሎች ሰዎች የተለያዩ ነገሮችን ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ ሰው” (ምትክ ስም እና ተዛምዶአዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ዳቦ

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ዳቦ ለብዙ ሰዎች ምግብ ስለነበር በአጠቃላይ ምግብን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ግጭትና ስድብም ይቆማሉ

“ግጭት” እና “ስድብ” የሚሉት ረቂቅ ስሞች እንደ ግስ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች እርስ በርሳቸው ለወደፊት አይጨቃጨቁም ወይም እርስ በርሳቸው ለመጎዳዳት ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን አይናገሩም” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)