am_tn/pro/22/07.md

2.4 KiB

ይበደራል … ያበድራል

ይህንን መበደር ወይም ማበደር ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ገንዘብ ይበደራል … ገንዘብ ያበድራል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ኢፍትሐዊነትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፣

ጸሐፊው ሀይል የሌላቸውን ሰዎች በኢፍትሐዊነት ስለሚያሰቃዩ መሪዎች ወይም ሌሎች ሃያላን ሰዎች ሲናገር እነርሱ መከራ የሚያመጡ ዛፎችን የሚያበቅሉ ዘሮችን እንደዘሩ አድርጎ ገልጿቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰው ከእርሱ ይልቅ ሃይል የሌላቸውን ሰዎች በኢፍትሐዊነት ያሰቃያቸው እንደሆነ በኋላ መከራ ያመጡበታል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የቁጣውም በትር ይጠፋል

“በትር” የሚለው ቃል በሌሎች ሰዎች ላይ ላለን ሃይል ምትክ ስም ነው፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ኢፍትሐዊ መሪ ሌሎች ሰዎችን እንዲያሰቃይ የፈቀደለትን ስልጣን ያጣዋል ወይም 2) እርሱ ለፈጸመው ኢፍትሐዊነት ሰዎች እርሱን በመጉዳት ምላሽ ሲሰጡ እነርሱን ለማስቆም የሚችልበት ምንም ዓይነት ሃይል አይኖረውም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎችን ለመጉዳት የተጠቀመበት ሃይል ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ አይኖረውም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የቁጣው በትር

“በትር” የሚለው ቃል በሌሎች ሰዎች ላይ ላለን ስልጣን ምትክ ስም ነው፡፡ ኢፍትሐዊ ሰው በንጹሃን ሰዎች ላይ በጣም እንደተቆጣ ያህል እነርሱን ሲጎዳቸው ነበር፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎችን እንደሚቀጣ ይጠቀምበት የነበረ በትር” ወይም “ሌሎችን ለመጉዳት የተጠቀመበት ሃይል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ይጠፋል

“ይጠፋል” ተብሎ የተተረጎመው ቃል እጽዋት ሲደርቁም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡