am_tn/pro/21/30.md

2.0 KiB

ጥበብ የለም፣ ማስተዋል የለም እና ምክር የለም

“የለም” የሚለው ቃል የተደጋገመው ረቂቅ ስም ለሆኑት “ጥበብ፣” “ማስተዋል” እና “ምክር” አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ማንኛውም ሰው ሊያውቅ ወይም ሊያስብ ወይም ሊናገር ከሚችለው ማንኛውም ነገር ይበልጣል፡፡ በአንተ ቋንቋ “የለም” የሚለው ቃል እንዲደጋገም አያስፈልገውም ይሆናል፡፡ ይህ ረቂቅ ስም እንደ ቅጽል ወይም ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበበኛ ሰው የለም፣ ነገሮችን የሚያስተውል አንድም ሰው የለም እና ለሌሎች ምን መስራት እንዳለባቸውና ማን መስራት እንደሚገባው የሚነግራቸው አንድም ሰው የለም” ወይም “ጥበብ፣ ማስተዋል ወይም ምክር የለም” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን ሊቋቋም የሚችል

“እግዚአብሔርን የሚያሸንፍ” ወይም “እግዚአብሔር ሊሰራ ከሚፈልገው በተቃራኒ የሚሰራ” ወይም “እርሱ ትክክል እግዚአብሔር ግን ስህተት እንደሆነ ሊያሳይ የሚችል”

ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል

እነዚህ ቃላት በገቢር ቅርጽ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወታደሮች ለጦርነት ቀን ያዘጋጃሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የጦርት ቀን

“ቀን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከቀን ለሚያጥር ወይም ለሚረዝም ጊዜ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጦርነት በሚኖርበት ጊዜ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)